ምን ታመጣላችሁ? (Re)
(መላኩ የእናት ልጅ) * * * * * የኢትዮጵያ ልጆች እናንተ ሁላችሁ ከውስጤ፣ ከልቤ ውድድድ…ባደርጋችሁ ከመወደድ ሌላ ምን ታመጣላችሁ! * * * * * ሃይማኖቴን ተውት ብሔሬንም ተውት ቀለሜንም ተውት እውቀቴምን ተውት ይህ የእኔ ጉዳይ ነው ፍቅሬ ያለላችሁ “ሰውነቴ” ላይ ነው እዩት እኔነቴን እንደናንተው ሰው ነኝ ፍቅርን በመስጠት ፍቅርን የማገኝ የሰውነት ክብሬን ብቻ ተመልከቱ ወደ ፍቅር ግቡ ከእስራት ተፈቱ እኔ ግን እመኑኝ ሰው ስለሆናችሁ ሰው በመሆኔ ነው ከልብ ‘ምወዳችሁ ስላፈቀርኋችሁ ምን ታመጣላችሁ? * * * * * ከየትም ብሔር ኑ በምንም ስም ተጠሩ የትም ቦታ ኑሩ ከቶ ቢኖራችሁ ምንም ዓይነት ቀለም አትጠራጠሩ አንድ ነው የእኛ ደም የሁሉም ሰው ደሙ ቀይ ብቻ እኮ ነው የዘር መለያየት መንስኤው ምንድነው? በአንድ አገር ጥላ ሥር ምንኖር ተጠልለን ተፈጥሮ ነውና- በብዙ መንገዶች እንለያያለን ግን ምን ያግደናል? ከልብ ለመዋደድ ከልብ ለመፋቀር በአንዲት አገር ጥላ- ንፍቅፍቅ እያሉ- ባንድ አብሮ ለመኖር የራሳችሁ ጉዳይ! ካልወደዳችሁኝ- ያው ቀረሁባችሁ እኔ ግን ከልቤ- እኔም ሰው ነኝና ሰው በመሆናችሁ እወዳችኋለሁ! አፈቅራችኋለሁ! ምን ታመጣላችሁ? ………………….(ግንቦት 11/2006)
1 Comment
|
Archives
June 2019
Categories |